Clergy
HOME
Board of Turstees
Sunday School
Events
Contact us

Membership Registration Form

የአባልነት መመዝገቢያ ቅጽ

Membership Registration

የአባልነት ምዝገባ

Welcome, and thank you for your desire to become a member of St. Mary Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. Membership in the Church is a sacred commitment to grow in faith, participate in the life of the Church, and live according to the teachings of our Lord Jesus it is written in Psalm 133:1, "How good and pleasant it is when God’s people live together in unity!" By completing this form, you are expressing your willingness to join our church family, take part in worship, and support the mission of the Church. We are many members, but as Romans 12:5 reminds us, "In Christ we, though many, form one body, and each member belongs to all the others."We invite you to uphold the faith and traditions of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, as we strive together to be "rooted and built up in Him, strengthened in the faith as you were taught, and overflowing with thankfulness" (Colossians 2:7).May God bless you as you take this important step in your spiritual journey.Registration ChecklistTo complete your official registration, please ensure you have the following ready:Family Details: Full names and ages for spouses and children under 21.Contribution: Select your monthly stewardship level (starting from $10).Photo: A family photo for the church records (optional but encouraged).Signature: Your digital agreement to uphold the Tewahedo faith and traditions."Each of you should use whatever gift you have received to serve others, as faithful stewards of God’s grace." — 1 Peter 4:10

የአባልነት ምዝገባ

እንኳን ወደ ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአባልነት ምዝገባ በደህና መጡ። በቤተ ክርስቲያን አባል መሆን ከሚጠቅመን ዋና ዋና ነገሮች አንዱ በእምነት ለማደግ፣ በቤተ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ለመሳተፍ እና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት መሠረት ለመኖር እንድንችል ስለሚረዳን እና እኛም በአባልነታችን በምናደርጋቸው አገልግሎቶች የሰማያዊ በረከት ተሳታፊ ስለሚያደርገን ጭምር ነው ይህ ደግሞ መንፈሳዊ መታደልነው።

አምላካችን እግዚኣብሔር አስቀድሞ ቅዱስ ዳዊት እንደተናገረ በመዝሙር 133:1 ላይ "ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው!" ተብሎ እንደተጻፈ፤ እርስዎም ይህንን ቅጽ በመሙላት የቤተ ክርስቲያናችን ቤተሰብ አባል ለመሆን፣ በአምልኮ ለመሳተፍ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ተልእኮ ለመደገፍ ያለዎትን ፈቃደኝነት ይገልጹ ዘንድ መንፈሳዊ ጥሪያችነን እናቀርብልዎታለን።

ሐዋርያምው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳስተማረን በቤተ ክርስቲያን አንድነት ጉባዔ ስንሳተፍና ህብረት ሲኖረን ይህ አንድነትና ህብረት ከአምላካችን ከእየሱስ ክርስቶስ ጋር አንድ የሚያደርግ ነው ፣ ሮሜ 12:5 "እንዲሁ እኛ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው ብልቶች ነን።"

በእምነት "ሥር ሰዳችሁና ታንጻችሁ፥ እንደ ተማራችሁትም በእምነት ጸንታችሁ፥ ምስጋናም ይብዛላችሁ" (ቆላስይስ 2:7) ተብሎ እንደተጻፈው ሁሉ፤ እያንዳንዳችን በዚህ የመመዝገቢያ ቅጽ ተመዝግባችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እምነትና ትውፊት እንድትጠብቁ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

የምዝገባ ቅድመ-ሁኔታዎች (Checklist)

ይፋዊ ምዝገባውን ለማጠናቀቅ እባክዎ የሚከተሉት ዝግጁ መሆናቸውን ያረጋግጡ፦

የቤተሰብ ዝርዝር፦ የትዳር አጋር እና ዕድሜያቸው ከ21 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ሙሉ ስም እና ዕድሜ።

መዋጮ፦ ወርሃዊ የአባልነት መዋጮ መጠንዎን ይምረጡ (ከ$10 ጀምሮ)።

ፎቶ፦ ለቤተ ክርስቲያን መዝገብ የሚሆን የቤተሰብ ፎቶ (ግዴታ ባይሆንም ይበረታታል)።

ፊርማ፦ የተዋሕዶ እምነትንና ትውፊትን ለመጠበቅ የሚገቡት ዲጂታል ስምምነት።

"እያንዳንዱ እንደ ተቀበለው የጸጋ ስጦታ መጠን እግዚአብሔርን ልዩ ልዩ ጸጋ እንደ ጥሩ መጋቢዎች እርስ በርሳችሁ አገልግሉ" — 1 ጴጥሮስ 4:10

Announcement/ማስታወቂያ

Easter Celebration/የትንሣኤ በዓል

የትንሣኤ በዓል የሚከበረው ሚያዝያ ፬ ቀን ፪ሺ፲፰ዓ/ም ነው እርስዎም የጌታችንን የመድኃኒታችንን የእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤውን በዓል ከእኛ ጋር በደመቀ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርአት ያክብሩ

The Feast of the Resurrection (Easter) will be celebrated on Miyazya 4, 2018 E.C.

You are invited to join us in celebrating the Resurrection of our Lord and Savior Jesus Christ with a joyful and reverent spiritual service.

Easter Celebration/የትንሣኤ በዓል

የትንሣኤ በዓል የሚከበረው ሚያዝያ ፬ ቀን ፪ሺ፲፰ዓ/ም ነው እርስዎም የጌታችንን የመድኃኒታችንን የእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤውን በዓል ከእኛ ጋር በደመቀ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርአት ያክብሩ

The Feast of the Resurrection (Easter) will be celebrated on Miyazya 4, 2018 E.C.

You are invited to join us in celebrating the Resurrection of our Lord and Savior Jesus Christ with a joyful and reverent spiritual service.