የቅድስት ማርያም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሎስ አንጀለስ 

አጭር ታሪክ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ መንፈሳዊ አገልግሎት በሎስ አንጀለስ ከተማ የሰጠው በ1972 ዓ. ም. (1979) ነበር። አገልግሎቱም የተሰጠው በአቡነ ይስሃቅ ስልጣነ ክህነት በተቀበሉና ኢትዮጵያውያን ባልሆኑ ዲያቆናት ነበር። ከነዚህም አንዱ ዲያቆን ገብረ ፃድቅ የሚባለው ነበር። የቤተክርስቲያኑም ስም ተክለሃይማኖት ነበር። ከዚያም ኢትዮጵያኖች መሰባሰብ ሲጀምሩ አባ ነሲቡ (ተክለ ሚካኤል) ከቺካጎ መጥተው ምእመናኑም ቁጥር በመጨመሩ እንቅስቃሴ ተጀምሮ የእርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቋመ። ይህ ኮሚቴ መተዳደሪ ደንብ ነደፈ። እዚህ ኮሚቴ ውስጥ ወ/ሮ መሠረት የማነ፣ አቶ ጌትነት አለበልና እማሆይ እየሩሳሌም ደሕኔ ነበሩበት። 

በቆዩት አፍሪካ-አሜሪካኖችና በኢትዮጵያን መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ ተለያዩና፣ ኢትዮጵያውያኑ ከግብጽ ቤተክርስቲያን በጥገኝነት ቅዳሜ-ቅዳሜ ስርዓተ ቅዳሴ ማካሄድ ተጀመረ። የቤተክርስቲያኗም ስም ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተብሎ እንዲሰየም ተወሰነ። አዲስ የስራ አስኪያጅ ኮሚቴም ተቋቋመ። የቤተክርስቲያኗ የስራ አስኪያጅ አባል የሆኑት እማሆይ እየሩሳሌም አቶ ጌትነትና ወ/ሮ መሠረት የዚህ ኮሚቴ አባላት ነበሩ። በሕይወት የሌሉ ደግሞ አቶ ኃይለ ጊዮርጊስ አስፋውና አቶ ፈቃደ ስላሴ መስፍን የዚህ ኮሚቴ አባላት ነበሩ።

በ1981 ዓ. ም. በኮክራን ጎዳና በሚገኝ አንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ በጥገኝነት አገልግሎት መስጠቱ ቀጠለ። ይህ ሁሉ ሲሆን ጊዜያዊ አገልጋይ እንጅ በቋሚነት የሚሰራ ካህን አልነበረም። ለመጀመሪያ ጊዜ በቋሚነት የሚያገለግሉ ካህን አባ ወልደ ሠማያት ከሱዳን የመጡት በዚህ ወቅት ነበር። ቀጥሎም አባ መንግሥቱ ከእስራኤል መጡ። ቀሲስ አማረ መንግሥቱም ተጨመሩ። በመጀመሪያው አካባቢ አቡነ ይስሃቅም ሆኑ አባ ጳውሎስ ከኒው ዮርክ (በኋላ አቡነ ጳውሎስ) አልፎ-አልፎ እየመጡ ያገለግሉ ነበር። 

አባ ጳውሎስ በቋሚነት እንዲመጡ በፈለጉና፣ አይምጡብን በሚሉ መካከል ልዩነት ተነሳ፤ አለመግባባቶች ተባብሰው ጠቅላላ ስብሰባ ተጠርቶ ምእመናኑ መስማማት አቅቷቸው ከሁለት ተከፈሉ። አንደኛው ክፍል ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ጥንታዊ ቤተክርስቲያን (ያሁኑ ድንግል ማርያም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን) ተብለው ተከፈሉ። ሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት “ኦርቶዶክስ ተዋህዶ” የሚለውን ሃረግ መጠቀምን በሚመለከት ለብዙ ዓመታት በፍርድ ቤት ሲሟገቱ ከቆዩ በኋላ በ2000 ዓ. ም. የሁለቱ ቤትክርስቲያኖች ቦርዶች ከብዙ ያጋራ ስብሰባዎች በኋላ እርቅ እንዲወርድ አድርገዋል። በዚህ ሂደት ላይ ምእመናኑ በተለይም መዘምራን ድጋፍ በመስጠትና እርቁን በመደገፍ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። 

1988-1999 ያገለገሉ የቦርድ አባሎች

አቶ አቡኔ ብሩ

አቶ ብርሃኔ የማነ

ወ/ት ንግሥት ቦጋለ

ወ/ሮ አስናቀች ፍርድ አወቅ

አቶ ዘውዱ መርሻ 

ወ/ሮ ጥሩ ወርቅ መስፍን

ወ/ሮ አካሌ የማነ

አቶ ምስማክ ተ/ጊዮርጊስ

አቶ መስፍን ዓለሙ                          

አቶ ታዲዎስ አሉላ

ወ/ሮ አምሳለ ወርቅ ኃ/ማርያም                 

ወ/ት ዓለሜ የማነ

አቶ ሃብተወልድ ካሳ                       

ወ/ሮ መንበረ መክብብ

አቶ በትሩ ው/ትንሳኤ                          

ወ/ት ሃይማኖት ፈቃዱ

ወ/ሮ አሰፋሽ ኪዳኔ

ዶ/ር መስፍን ዓለማየሁ

1999 - 2019 ያገለገሉ የቦርድ አባሎች

አቶ ታዲዎስ አሉላ 

ወ/ሮ መንበረ መክብብ 

ወ/ሮ አስናቀች ፍርድ አወቅ 

ዶር መስፍን ዓለማየሁ 

አቶ ተስፋዬ ክንፈ 

አቶ ዘውዱ በላይ 

አቶ አቡኔ ብሩ 

አቶ ፀጋ ምንተስኖት 

አቶ አጥናፉ ታሪኩ 

አቶ ተስፋዬ ዉድነህ 

አቶ ገነነ ልዑል ሰገድ 

አቶ ዳዊት ስለሞን 

ወ/ሮ ነገደ ገዛኸኝ 

ዶ/ር መሰለ ነጋሽ 

ሲስተር አምሳለ መንክር 

አቶ ሄኖክ ታፈሰ 

አቶ ንጉሡ ወልደ ገብርኤል 

አቶ አልማው ዮሃን

ከ1984-1987 ያገለገሉ የቤተክርስቲያኗ በህይወት ያሉና በሞት የተለዩ  የቦርድ አባሎች

ወ/ሮ መንበረ ፀሐይ ኃይለ ጊዮርጊስ

አቶ ፈቃደ ሥላሴ መስፍን 

አቶ ጌትነት አለበል

ወ/ሮ መሠረት የማነ

አቶ ሞገስ ሺፈራው

አቶ ዲቡ ወልዴ

አቶ አርአያ ጎበዜ 

እማሆይ እየሩሳሌም ደህኔ 

አቶ ሠለሞን ገሠሠ 

አቶ ኃይለ ጊዮርጊስ አስፋው