ቅድስት ድንግል ማርያም በክርስትና ታሪክ ውስጥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናት፣ እንዲሁም የንጽሕና፣ የትሕትና እና የታማኝነት ፍጹም አርአያ ተደርጋ ትከበራለች። ለእግዚአብሔር ጥሪ በሰጠችው ቅዱስ "እሺታ" (ይሁንልኝ) አማካኝነት፣ የአለም መድኃኒት ክርስቶስ በሥጋ ተገልጦ ለሰው ልጆች ሁሉ የድኅነት ተስፋን አምጥቷል። ምዕመናንም በእናትነት ፍቅሯና በማይነጥፍ ጸሎቷ በመታመን፣ ወደ ልጇ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትመራቸው አፍቃሪ አማላጅነቷን ይሻሉ፤ እርሷም በልጇ ዘንድ ባላት ሞገስ የልባቸውን በጎ መሻት ትፈጽማለች።
"አሕዛብ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል።" (ሉቃስ 1:48)
The Blessed Virgin Mary is honored throughout Christian history as the Mother of our Lord Jesus Christ and the supreme model of faith, humility, and obedience. Through her faithful "Yes" (Fiat) to God’s divine call, Christ entered the world, bringing the light of salvation and eternal hope to all humanity. Believers look to her with deep devotion, seeking her maternal intercession and guidance as she leads them closer to her Son. Through the grace bestowed upon her, she remains a compassionate advocate for all who seek her prayers with a sincere heart.
"For behold, henceforth all generations will call me blessed." (Luke 1:48)
የእንኳን ደህና መጡ መልእክት
ወደ ጽርሐ አርያም ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንኳን በሰላም መጡ! ቤተ ክርስቲያናችን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ትውፊት፣ ታሪክና ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮን መሠረት በማድረግ
ዘወትር መንፈሳዊ አገልግሎት ትሰጣለች።
አገልግሎቶቻችን፦
የጸሎትና የቅዳሴ አገልግሎት፦ ዘወትር ጧት ከ11:00 ሰዓት ጀምሮ ጸሎተ ኪዳን የሚደርስ ሲሆን፣ በየሳምንቱ እሁድና በበዓላት ቀናት ደግሞ የቅዳሴ ሥርዓተ አምልኮ ይፈጸማል።
ክብረ በዓላት፦ የእመቤታችንን የልደት በዓል (ግንቦት 1)፣ የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማን ዓመታዊ በዓል እንዲሁም የነሐሴ ኪዳነ ምሕረትን በደመቀ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓት እናከብራለን።
የሰንበት ትምህርት ቤት፦ ለልጆቻችን ዘወትር ቅዳሜ ከሰዓት 8:00 ሰዓት ጀምሮ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርትና የግብረ ዲቁና ሥልጠና እንሰጣለን። በእሁድ መደበኛ አገልግሎት ደግሞ እንደየደረጃቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ይሰጣል።
የምክር አገልግሎት፦ ለአባላቶቻችን መንፈሳዊ የምክር አገልግሎት እንሰጣለን።
ኑና ከእኛ ጋር በቤተ ክርስቲያናችን በረከት ተሳተፉ!
"ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ።" (መዝሙር 122:1)
Welcome Message
Welcome to St. Mary Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. Our parish is a vibrant spiritual community dedicated to preserving the ancient traditions, history, and teachings of the Ethiopian Orthodox Tewahedo faith.
Our Services:
Worship & Liturgy: We conduct daily Kidane (Covenant Prayer) starting at 5:00 AM. Every Sunday and on holy feast days, we celebrate the Divine Liturgy (Kidase) to glorify God and receive His grace.
Annual Feasts: We joyfully celebrate major feast days, including the Nativity of the Blessed Virgin Mary (Lideta), the martyrdom of Saint Arsema, and the Covenant of Mercy (Kidane Meheret) in August.
Sunday School: We are committed to nurturing our youth. Every Saturday starting at 2:00 PM, we offer Amharic language classes and Deaconship training. On Sundays, children receive age-appropriate Bible lessons.
Spiritual Guidance: We provide pastoral counseling and spiritual support to all our members.
We warmly invite you and your family to join us and experience the peace and blessings of the Lord.
"I was glad when they said to me, ‘Let us go into the house of the Lord.’" (Psalm 122:1)
Feast of Lideta Maryam
የልደታ በዓል የእመቤታችን የልደት በአል በደመቀ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርአት ቅዳሜ ግንቦት ፩ ቀን ፪ሺ፲፰ ዓ/ም ከበራል እርስዎም የበአሉ በረከት ተካፋይ እንዲሆኑ በአክብሮት ተጋብዘዋል።
The Feast of Lideta Maryam for the year 2018 E.C. will be celebrated on Saturday, May 9, 2026 with a joyful and reverent spiritual ceremony.You are warmly invited to join us and be part of this blessed celebration.
Stay Connected with St. Mary’s Ethiopian Orthodox Tewahedo Church via Text
Fill out the form to receive our text alerts.

